caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 70

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:70

وَذَرِ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ دِينَهُمْ لَعِبًا وَلَهْوًا وَغَرَّتْهُمُ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا وَذَكِّرْ بِهِۦٓ أَن تُبْسَلَ نَفْسٌۢ بِمَا كَسَبَتْ لَيْسَ لَهَا مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلِىٌّ وَلَا شَفِيعٌ وَإِن تَعْدِلْ كُلَّ عَدْلٍ لَّا يُؤْخَذْ مِنْهَآ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ أُبْسِلُوا۟ بِمَا كَسَبُوا۟ لَهُمْ شَرَابٌ مِّنْ حَمِيمٍ وَعَذَابٌ أَلِيمٌۢ بِمَا كَانُوا۟ يَكْفُرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy70. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም ሃይማኖታቸውን ጨዋታና ቀልድ አድርገው የያዙትንና ቅርቢቱ ሕይወት ያታለለቻቸውን ተዋቸው:: ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ እንዳትጠፋ በእርሱ (በቁርአን) አስታውስ:: ለእርሷ ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ አማላጅ ማንም የላትም:: ፊዳ የተባለን ሁሉ ብትከፍል እንኳን ተቀባይነት የላትም:: እነዚያ በሰሩት ስራ የተጠፉት ናቸው:: በክህደታቸው ምክንያት ከፈላ ውሃ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያንም ሃይማኖታቸውን ጨዋታና ላግጣ አድርገው የያዙትን ቅርቢቱም ሕይወት ያታለለቻቸውን ተዋቸው፡፡ በእርሱም (በቁርኣን) ነፍስ በሠራችው ሥራ እንዳትጠፋ አስታውስ፡፡ ለእርሷ ከአላህ ሌላ ረዳትና አማላጅ የላትም፡፡ በመበዢያም ሁሉ ብትበዥ ከርሷ አይወሰድም፡፡ እነዚህ እነዚያ በሠሩት ሥራ የተጠፉት ናቸው፡፡ ለነሱ ይክዱ በነበሩት ምክንያት ከፈላ ውሃ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70