caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 71

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:71

قُلْ أَنَدْعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُنَا وَلَا يَضُرُّنَا وَنُرَدُّ عَلَىٰٓ أَعْقَابِنَا بَعْدَ إِذْ هَدَىٰنَا ٱللَّهُ كَٱلَّذِى ٱسْتَهْوَتْهُ ٱلشَّيَٰطِينُ فِى ٱلْأَرْضِ حَيْرَانَ لَهُۥٓ أَصْحَٰبٌ يَدْعُونَهُۥٓ إِلَى ٱلْهُدَى ٱئْتِنَا قُلْ إِنَّ هُدَى ٱللَّهِ هُوَ ٱلْهُدَىٰ وَأُمِرْنَا لِنُسْلِمَ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ ሌላ የማይጠቅምንና የማይጎዳን እንገዛለን? አላህ በቀናው መንገድ ከመራን በኋላ የኋሊት እንመለሳለን? እንደዚያ በምድር ላይ የዋለለ ሲሆን ሰይጣናት አሳስተውት ለእርሱ ‹ወደ እኛ ና› እያሉ ወደ ቅን መንገድ የሚጠሩ ወዳጆች ቢኖሩትም (እንደማይከተላቸው) እንሆናለንን?» በላቸው:: «የአላህ መንገድ ቀጥተኛው መንገድ ነው:: ለዓለማት ጌታ ልንገዛም ታዘዝን።» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ከአላህ ሌላ የማይጠቅመንን እና የማይጎዳንን እንገዛለን አላህም ከመራን ጊዜ በኋላ የኋሊት እንመለሳለን እንደዚያ በምድር ላይ የዋለለ ሲኾን ሰይጣናት እንዳሳሳቱት ለእርሱ ወደኛ ና እያሉ ወደ ቅን መንገድ የሚጠሩ ወዳጆች እንዳሉት (እንደማይከተላቸውም) ሰው እንኾናለን?» በላቸው፡፡ «የአላህ መንገድ እርሱ ቀጥተኛው መንገድ ነው፡፡ ለዓለማት ጌታ ልንገዛም ታዘዝን» በላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70