وَلَقَدْ جِئْتُمُونَا فُرَٰدَىٰ كَمَا خَلَقْنَٰكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ وَتَرَكْتُم مَّا خَوَّلْنَٰكُمْ وَرَآءَ ظُهُورِكُمْ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَآءَكُمُ ٱلَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَٰٓؤُا۟ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy94. «በመጀመሪያ ጊዜ ልክ እንደፈጠርናችሁ ሆናችሁ የሰጠናችሁን ሁሉ ከጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትሆኑ ለየብቻችሁ ሆናችሁ በእርግጥ ወደ እኛ መጣችሁ:: እነዚያንም እነርሱ በእናንተ (ጉዳይ) ለአላህ ተጋሪዎቹ ናቸው:: የምትሏቸውን አማላጆቻችሁን ከናንተ ጋር አናይም:: ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ:: ከናንተም ያ ያማልደናል የምትሉት ሁሉ ጠፋ» (ይባላሉ።)
Amharic Translation - Muhammad Sadiqመጀመሪያም ጊዜ እንደ ፈጠርናችሁ ኾናችሁ የሰጠናችሁን ሁሉ በጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትኾኑ ለየብቻችሁ ኾናችሁ በእርግጥ መጣችሁን እነዚያንም እነሱ በእናንተ ውስጥ (ለአላህ) ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፡፡ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ (ያማልደናል) የምትሉት ጠፋ (ይባላሉ)፡፡