caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 93

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:93

وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوْ قَالَ أُوحِىَ إِلَىَّ وَلَمْ يُوحَ إِلَيْهِ شَىْءٌ وَمَن قَالَ سَأُنزِلُ مِثْلَ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ وَلَوْ تَرَىٰٓ إِذِ ٱلظَّٰلِمُونَ فِى غَمَرَٰتِ ٱلْمَوْتِ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ بَاسِطُوٓا۟ أَيْدِيهِمْ أَخْرِجُوٓا۟ أَنفُسَكُمُ ٱلْيَوْمَ تُجْزَوْنَ عَذَابَ ٱلْهُونِ بِمَا كُنتُمْ تَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ غَيْرَ ٱلْحَقِّ وَكُنتُمْ عَنْ ءَايَٰتِهِۦ تَسْتَكْبِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy93. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም ወደ እርሱ ምንም ያልተወረደለት ሲሆን «ወደ እኔ ተወረደልኝ።» ካለና «አላህ ያወረደውን አይነት ማውረድም በእርግጥ እችላለሁ።» ካለ ይበልጥ እራሱን በዳይ ማን ነው? በደለኞችን በሞት መከራዎች ውስጥ በሆኑ ጊዜ መላዕክት እጆቻቸውን ዘርጊዎች ሆነው (ለቅጥጥብ) «ነፍሶቻችሁን አውጡ:: ከአላህ ላይ እውነትን ያልሆነን ነገር ትናገሩም የነበራችሁና በአናቅጽም ላይ ትኮሩ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬ የውርደት ቅጣት ትመነዳላችሁ» በሚሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ባየህ ነበር)::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበአላህም ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይም ወደርሱ ምንም ያልተወረደለት ሲኾን «ወደኔ ተወረደልኝ» ካለና፡-«አላህም ያወረደውን ብጤ በእርግጥ አወርዳለሁ» ካለ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው በደለኞችንም በሞት መከራዎች ውስጥ በኾኑ ጊዜ መላእክት እጆቻቸውን ዘርጊዎች ኾነው « (ለቅጥጥብ) ነፍሶቻችሁን አውጡ፤ በአላህ ላይ እውነት ያልኾነን ነገር ትናገሩ በነበራችሁትና ከአንቀጾቹም ትኮሩ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ» (የሚሏቸው ሲኾኑ) ብታይ ኖሮ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70