caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 128

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:128

وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا يَٰمَعْشَرَ ٱلْجِنِّ قَدِ ٱسْتَكْثَرْتُم مِّنَ ٱلْإِنسِ وَقَالَ أَوْلِيَآؤُهُم مِّنَ ٱلْإِنسِ رَبَّنَا ٱسْتَمْتَعَ بَعْضُنَا بِبَعْضٍ وَبَلَغْنَآ أَجَلَنَا ٱلَّذِىٓ أَجَّلْتَ لَنَا قَالَ ٱلنَّارُ مَثْوَىٰكُمْ خَٰلِدِينَ فِيهَآ إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሁሉንም በአንድ ቦታ በሚሰበስባቸው ቀን የሚሆነውን አስታውስ:: «የአጋንንት ቡድኖች ሆይ! ከሰዎች ቡድንን በማጥመም በእርግጥ አበዛችሁ።» ይባላሉ:: ከሰዎችም መካከል የሆኑት ወዳጆቻቸው «ጌታችን ሆይ! ከፊላችን በከፊሉ ተጠቀመ:: ያንን ለእኛ የወሰንክልንን ጊዜያችንን ደረስን።» ይላሉ:: «እሳቲቱ አላህ የሻው ጊዜ ሲቀር በውስጧ ዘወታሪዎች ስትሆኑ መኖሪያችሁ ናት።» ይላቸዋል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ጥበበኛና አዋቂ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሁሉንም የሚሰበስብባቸውንም ቀን (አስታውስ)፡፡፡ የአጋንንት ጭፍሮች ሆይ! ከሰዎች (ጭፍራን በማጥመም) በእርግጥ አበዛችሁ (ይባላሉ)፡፡ ከሰዎችም የኾኑት ወዳጆቻቸው፡-«ጌታችን ሆይ! ከፊላችን በከፊሉ ተጠቀመ፡፡ ያንንም ለእኛ የወሰንክልንን ጊዜያችንን ደረስን» ይላሉ፡፡ እሳት መኖሪያችሁ ናት አላህ የሻው ጊዜ ሲቀር በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ ይላቸዋል፡፡ ጌታህ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70