وَمَا قَدَرُوا۟ ٱللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِۦٓ إِذْ قَالُوا۟ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَىٰ بَشَرٍ مِّن شَىْءٍ قُلْ مَنْ أَنزَلَ ٱلْكِتَٰبَ ٱلَّذِى جَآءَ بِهِۦ مُوسَىٰ نُورًا وَهُدًى لِّلنَّاسِ تَجْعَلُونَهُۥ قَرَاطِيسَ تُبْدُونَهَا وَتُخْفُونَ كَثِيرًا وَعُلِّمْتُم مَّا لَمْ تَعْلَمُوٓا۟ أَنتُمْ وَلَآ ءَابَآؤُكُمْ قُلِ ٱللَّهُ ثُمَّ ذَرْهُمْ فِى خَوْضِهِمْ يَلْعَبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy91. (ከሓዲያን) «አላህ በሰው ላይ ምንም አላወረደም።» ባሉ ጊዜ አላህን ተገቢውን ክብሩን አላከበሩትም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዲህ በላቸው «ያንን ለሰዎች ብርሃንና ቅን መመሪያ ሆኖ ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትሆኑ ማን አወረደው? (የወደዳችኋትን) ትገልጿታላችሁ ብዙውንም ትደብቃላችሁ፤ እናንተም ሆናችሁ አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ::» (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ አወረደው።» በላቸው:: ከዚያም በውሸታቸው ውስጥ የሚጫወቱ ሲሆኑ ተዋቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«አላህ በሰው ላይ ምንም አላወረደም» ባሉም ጊዜ አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም፡፡ (እንዲህ) በላቸው፡- «ያንን ብርሃንና ለሰዎች መሪ ኾኖ ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትኾኑ ማን አወረደው (የወደዳችኋትን) ትገልጿታላችሁ ብዙውንም ትደብቃላችሁ፡፡ እናንተም አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ፤«አላህ (አወረደው)» በላቸው፡፡ ከዚያም በውሸታቸው ውስጥ የሚጫወቱ ሲኾኑ ተዋቸው፡፡