caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 138

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:138

وَقَالُوا۟ هَٰذِهِۦٓ أَنْعَٰمٌ وَحَرْثٌ حِجْرٌ لَّا يَطْعَمُهَآ إِلَّا مَن نَّشَآءُ بِزَعْمِهِمْ وَأَنْعَٰمٌ حُرِّمَتْ ظُهُورُهَا وَأَنْعَٰمٌ لَّا يَذْكُرُونَ ٱسْمَ ٱللَّهِ عَلَيْهَا ٱفْتِرَآءً عَلَيْهِ سَيَجْزِيهِم بِمَا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy138. በሀሳባቸውም «እነዚህ እርም የሆኑ ለማዳ እንሰሳና አዝመራ ናቸው:: የምንሻለት ሰው እንጂ ሌላ ማንም አይበላቸዉም:: እነዚህ ደግሞ ጀርባዎቻቸው እርም የተደረገ ለማዳ እንሰሳ ናቸው:: አይጫኑም:: እነዚህ ሲታረዱ በእነርሱ ላይ የአላህን ስም የማይጠሩባቸዉም እንሳሳት ናቸው።» አሉ:: በእርሱ ላይ ለመቅጠፍ ነገሩን ወደ አላህ አስጠጉ:: ይቀጥፉት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣቸዋል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበሐሳባቸውም ይህች እርም የኾነች ለማዳ እንስሳና አዝመራ ናት፡፡ የምንሻው ሰው እንጂ ሌላ አይበላትም፡፡ (ይህች) ጀርቦችዋ እርም የተደረገች ለማዳ እንስሳም ናት (አትጫንም)፡፡ ይህች በርሷ ላይ የአላህን ስም (ስትታረድ) የማይጠሩባትም እንስሳ ናት አሉ፡፡ በእርሱ ላይ ለመቅጠፍ (ነገሩን ወደ አላህ አስጠጉ)፡፡ ይቀጥፉት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣቸዋል፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70