وَقَالُوا۟ مَا فِى بُطُونِ هَٰذِهِ ٱلْأَنْعَٰمِ خَالِصَةٌ لِّذُكُورِنَا وَمُحَرَّمٌ عَلَىٰٓ أَزْوَٰجِنَا وَإِن يَكُن مَّيْتَةً فَهُمْ فِيهِ شُرَكَآءُ سَيَجْزِيهِمْ وَصْفَهُمْ إِنَّهُۥ حَكِيمٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy139. «በእነዚህ እንስሳት ሆዶች ውስጥ ያለው ጽንሱ ሁሉ ለወንዶቻችን ብቻ በተለይ የተፈቀደ ነው:: በሚስቶቻችን ላይ ግን እርም የተደረገ ነው:: ሙት ሆኖ ቢወለድ ግን ወንዶቹም ሆነ ሴቶች በእርሱ ላይ ተጋሪዎች ናቸው።» አሉ:: ይህን በመቅጠፋቸው አላህ በእርግጥ ይቀጣቸዋል:: እርሱ ጥበበኛና አዋቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«በነዚህም እንስሶች ሆዶች ውስጥ ያለው ለወንዶቻችን በተለይ የተፈቀደ ነው፡፡ በሚስቶቻችን ላይ እርም የተደረገ ነው፡፡ ሙት ቢኾን (ሙት ኾኖ ቢወለድ) እነርሱ (ወንዶቹም ሴቶቹም) በርሱ ተጋሪዎች ናቸው» አሉ፡፡ በመቅጠፋቸው አላህ በእርግጥ ይቀጣቸዋል፡፡ እርሱ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡