وَكَذَٰلِكَ زَيَّنَ لِكَثِيرٍ مِّنَ ٱلْمُشْرِكِينَ قَتْلَ أَوْلَٰدِهِمْ شُرَكَآؤُهُمْ لِيُرْدُوهُمْ وَلِيَلْبِسُوا۟ عَلَيْهِمْ دِينَهُمْ وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ مَا فَعَلُوهُ فَذَرْهُمْ وَمَا يَفْتَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy137. ልክ እንደዚሁ ከአጋሪዎች ለብዙዎቹ ሊያጠፏቸውና ሀይማኖታቸውንም በነሱ ላይ ሊያቀላቅሉባቸው ዘንድ ልጆቻቸውን መግደልን ተጋሪዎቻቸው ጣኦታቱ አሳመሩላቸው:: አላህም በሻ ኖሮ (ይህን ጸያፍ ተግባር) ባልሰሩት ነበር:: እናም ከቅጥፈታቸው ጋር ተዋቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእንደዚሁም ከአጋሪዎቹ ለብዙዎቹ፤ ተጋሪዎቻቸው ሊያጠፉዋቸውና ሃይማኖታቸውንም በእነሱ ላይ ሊያቀላቅሉባቸው (ሊያመሳስሉባቸው) ልጆቻቸውን መግደልን አሳመሩላቸው፡፡ አላህም በሻ ኖሮ ባልሠሩት ነበር፡፡ ከቅጥፈታቸውም ጋር ተዋቸው፡፡