caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 136

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:136

وَجَعَلُوا۟ لِلَّهِ مِمَّا ذَرَأَ مِنَ ٱلْحَرْثِ وَٱلْأَنْعَٰمِ نَصِيبًا فَقَالُوا۟ هَٰذَا لِلَّهِ بِزَعْمِهِمْ وَهَٰذَا لِشُرَكَآئِنَا فَمَا كَانَ لِشُرَكَآئِهِمْ فَلَا يَصِلُ إِلَى ٱللَّهِ وَمَا كَانَ لِلَّهِ فَهُوَ يَصِلُ إِلَىٰ شُرَكَآئِهِمْ سَآءَ مَا يَحْكُمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy136. አጋሪዎች ለአላህ ከፈጠራቸው ፍጡራን ከአዝመራውም ከግመል፣ ከከብት፣ ከፍየል፤ ከበጉም ድርሻን አደረጉለት:: በሀሳባቸዉም «ይህ የአላህ ነው፤ ይህ ደግሞ ለተጋሪዎቻችን ነው።» አሉ። ለተጋሪዎቻቸው የሆነው ነገር ወደ አላህ ምንጊዜም አይደርስም:: ለአላህ የሆነው ነገር ግን ወደ ተጋሪዎቹ ይደርሳል አሉ። የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ!
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለአላህም ከፈጠረው ከአዝመራና ከግመል፣ ከከብት፣ ከፍየልም ድርሻን አደረጉ፡፡ በሐሳባቸውም «ይህ ለአላህ ነው፡፡ ይህም ለተጋሪዎቻችን ነው፡፡» ለተጋሪዎቻቸውም «(ለጣዖታት) የኾነው ነገር ወደ አላህ አይደርስም፡፡ ለአላህም የኾነው እርሱ ወደ ተጋሪዎቻቸው ይደርሳል» አሉ፡፡ የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ!
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70