وَإِذَا جَآءَتْهُمْ ءَايَةٌ قَالُوا۟ لَن نُّؤْمِنَ حَتَّىٰ نُؤْتَىٰ مِثْلَ مَآ أُوتِىَ رُسُلُ ٱللَّهِ ٱللَّهُ أَعْلَمُ حَيْثُ يَجْعَلُ رِسَالَتَهُۥ سَيُصِيبُ ٱلَّذِينَ أَجْرَمُوا۟ صَغَارٌ عِندَ ٱللَّهِ وَعَذَابٌ شَدِيدٌۢ بِمَا كَانُوا۟ يَمْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy124. ተዓምር በመጣላቸውም ጊዜ «የአላህ መልዕክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ:: አላህ መልዕክቱን የሚያደርግበትን ስፍራ አዋቂ ነው:: እነዚያን በአላህ ያመጹ ሰዎች ይዶልቱት በነበሩት ነገር አላህ ዘንድ ውርደትና ብርቱ ቅጣት ያገኛቸዋል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqተዓምርም በመጣቻቸው ጊዜ፡- «የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ፡፡ አላህ መልክቱን የሚያደርግበትን ስፍራ ዐዋቂ ነው፡፡ እነዚያን ያመጹትን ሰዎች ይዶልቱ በነበሩት ነገር አላህ ዘንድ ውርደትና ብርቱ ቅጣት ያገኛቸዋል፡፡