أَلَمْ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ مَا يَكُونُ مِن نَّجْوَىٰ ثَلَٰثَةٍ إِلَّا هُوَ رَابِعُهُمْ وَلَا خَمْسَةٍ إِلَّا هُوَ سَادِسُهُمْ وَلَآ أَدْنَىٰ مِن ذَٰلِكَ وَلَآ أَكْثَرَ إِلَّا هُوَ مَعَهُمْ أَيْنَ مَا كَانُوا۟ ثُمَّ يُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوا۟ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ إِنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ መሆኑን አታውቅምን? (በእውነቱ ሁሉንም አካቧል::) የሶስት ሰዎች መንሾካሾክ አይከሰትም፤ አላህ አራተኛው ቢሆን እንጂ፤ የአምስትም ሰዎች መንሾካሾክ አይከሰትም እርሱ ስድስተኛ ቢሆን እንጂ፤ ከዚያ ያነሰም ይሁን የበዛ ሰው መሾካሾክ አይከሰትም እርሱ ባሉበት ቦታ አብሯቸው ቢሆን እንጂ:: ከዚያ በትንሳኤ ቀን የሰሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል:: አላህ ሁሉን ነገር አዋቂ ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ በሰማያት ውስጥ ያለውን በምድርም ውሰጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ መኾኑን አታይምን? ከሦስት ሰዎች መሾካሾክ አይኖርም እርሱ አራተኛቸው ቢኾን እንጅ፡፡ ከአምስትም (አይኖርም) እርሱ ስድስተኛቸው ቢኾን እንጅ፡፡ ከዚያ ያነሰም የበዛም (አይኖርም) እርሱ የትም ቢኾኑ አብሯቸው ቢሆን እንጂ፡፡ ከዚያም በትንሣኤ ቀን የሠሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡ አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡