يَوْمَ يَبْعَثُهُمُ ٱللَّهُ جَمِيعًا فَيُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوٓا۟ أَحْصَىٰهُ ٱللَّهُ وَنَسُوهُ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ شَهِيدٌ
Amharic Translation - Africa Academy6. አላህ ሁላቸውንም በአንድ አድርጎ (አንድም ሳይቀር በአንድ ዓይነት) በሚቀሰቅሳቸው ቀን (ይቀጣቸዋል):: ከዚያም በዚህ ዓለም የሰሩትን ነገር ሁሉ ይነግራቸዋል:: እነርሱ የረሱት ሲሆን (መዝገባቸው ተመዝግቦ ያገኙታል) አላህ ግን አንድም ሳይቀር አውቆታል:: አላህ ሁሉንም ነገር ተመልካች ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ሁላቸውንም በሚቀስቃሳቸው ቀን (ይቀጣቸዋል)፡፡ የሠሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡ የረሱት ሲኾኑ አላህ ዐውቆታል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነው፡፡