أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ نُهُوا۟ عَنِ ٱلنَّجْوَىٰ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا نُهُوا۟ عَنْهُ وَيَتَنَٰجَوْنَ بِٱلْإِثْمِ وَٱلْعُدْوَٰنِ وَمَعْصِيَتِ ٱلرَّسُولِ وَإِذَا جَآءُوكَ حَيَّوْكَ بِمَا لَمْ يُحَيِّكَ بِهِ ٱللَّهُ وَيَقُولُونَ فِىٓ أَنفُسِهِمْ لَوْلَا يُعَذِّبُنَا ٱللَّهُ بِمَا نَقُولُ حَسْبُهُمْ جَهَنَّمُ يَصْلَوْنَهَا فَبِئْسَ ٱلْمَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ በመጥፎ ነገር ከመመሳጠር ወደ ተከለከሉት፤ ከዚያ ከእርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር የሚመለሱትንና በኃጢአት፣ በጠላትነትና መልዕክተኛውን በመቃወም ወደ ሚመሳጠሩ አላየህምን? (ሰላም ሊሉ) ወደ አንተ በመጡ ጊዜ አላህ ባላናገረህ ቃል ያናግሩሃል:: ውስጣቸው ይህ ሰው ነብይ ከሆነ በምንለው ነገር አላህ አይቀጣንም ኖሯልን? (ነብይ ከሆነስ) የለመነውን ነገር አላህ ተቀብሎት በሞትን ነበር ይላሉ:: ገሀነም የሚገቡባት ሲሆኑ ከአሁኑ ሞት ይልቅ በቂያቸው ናት:: ገሀነምም መመለሻነቷ ከፋች!
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደእነዚያ (በመጥፎ) ከመሾካሾክ ወደ ተከለከሉት፣ ከዚያም ከእርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር ወደሚመለሱት፣ በኃጢአትና ድንበር በማለፍ መልክተኛውን በመቃወም ወደሚንሾካሾኩት አላየህምን? (ሰላም ሊሉ) በመጡህም ጊዜ አላህ በእርሱ ባላናገረህ ቃል ያናግሩሃል፡፡ በነፍሶቻቸውም ውስጥ (ነቢይ ከኾንክ) «በምንለው ነገር አላህ አይቀጣንም ኖሮአልን?» ይላሉ፡፡ ገሀነም የሚገቧት ሲኾኑ በቂያቸው ናት፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!