caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Noor፣ አንቀጽ 40

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 102 · 24:40

أَوْ كَظُلُمَٰتٍ فِى بَحْرٍ لُّجِّىٍّ يَغْشَىٰهُ مَوْجٌ مِّن فَوْقِهِۦ مَوْجٌ مِّن فَوْقِهِۦ سَحَابٌ ظُلُمَٰتٌۢ بَعْضُهَا فَوْقَ بَعْضٍ إِذَآ أَخْرَجَ يَدَهُۥ لَمْ يَكَدْ يَرَىٰهَا وَمَن لَّمْ يَجْعَلِ ٱللَّهُ لَهُۥ نُورًا فَمَا لَهُۥ مِن نُّورٍ

Amharic Translation - Africa Academy40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወይም መጥፎ ስራዎቻቸው ከበላዩ ማዕበል ከበላዩ ደመና ያለበት ማዕበል በሚሸፍነው ጥልቅ ባህር ውስጥ እንዳሉ ጨለማዎች ነው:: እነዚያ ከፊላቸው ከከፊሉ በላይ ድርብርብ የሆኑ ጨለማዎች ናቸው:: በዚህች የተሞከረ ሰው እጁን ባወጣ ጊዜ ሊያያት አይደርስም:: አላህ ለእርሱ ብርሃንን ያላደረገለት ሰው ሁሉ ለእርሱ ምንጊዜም ምንም ብርሃን የለዉም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወይም (መጥፎ ሥራዎቻቸውን) ከበላዩ ደመና ያለበት ማዕበል በሚሸፈነው ጥልቅ ባህር ውስጥ እንዳሉ ጨለማዎች ነው፡፡ (እነዚያ) ከፊላቸው ከከፊሉ በላይ ድርብርብ የኾኑ ጨለማዎች ናቸው፡፡ (በዚህች) (የተሞከረ) (ሰው) እጁን ባወጣ ጊዜ ሊያያት አይቀርብም፡፡ አላህም ለእርሱ ብርሃንን ያላደረገለት ሰው ለእርሱ ምንም ብርሃን የለውም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70