caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Anfaal፣ አንቀጽ 42

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 88 · 8:42

إِذْ أَنتُم بِٱلْعُدْوَةِ ٱلدُّنْيَا وَهُم بِٱلْعُدْوَةِ ٱلْقُصْوَىٰ وَٱلرَّكْبُ أَسْفَلَ مِنكُمْ وَلَوْ تَوَاعَدتُّمْ لَٱخْتَلَفْتُمْ فِى ٱلْمِيعَٰدِ وَلَٰكِن لِّيَقْضِىَ ٱللَّهُ أَمْرًا كَانَ مَفْعُولًا لِّيَهْلِكَ مَنْ هَلَكَ عَنۢ بَيِّنَةٍ وَيَحْيَىٰ مَنْ حَىَّ عَنۢ بَيِّنَةٍ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَسَمِيعٌ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy42. (ሙስሊሞች ሆይ!) እናንተ በቅርቢቱ ዳርቻ ሁናችሁ እነርሱ ደግሞ በሩቂቱ ዳርቻ ሆነው የነጋዴዎቹም ቡድን ከናንተ በታች ሲሆኑ በሰፈራችሁ ጊዜ ያደረግንላችሁን አስታውሱ:: በተቃጠራችሁም ኖሮ ግን በቀጠሮው በተለያያችሁ ነበር:: ግን አላህ ሊሠራው የሚገባውን ነገር ሊፈጽምና የሚጠፋም ከአስረጅ መድረስ በኋላ እንዲጠፋ፤ ሕያው የሚሆንም ከአስረጅ መድረስ በኋላ ሕያው እንዲሆን ያለቀጠሮ አጋጠማችሁ:: አላህ በእርግጥ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ በቅርቢቱ ዳርቻ ኾናችሁ እነርሱም በሩቂቱ ዳርቻ ኾነው የነጋዴዎቹም ጭፍራ ከናንተ በታች ሲኾኑ በሰፈራችሁ ጊዜ (ያደረግንላችሁን አስታውሱ)፡፡ በተቃጠራችሁም ኖሮ በቀጠሮው በተለያያችሁ ነበር፡፡ ግን አላህ ሊሠራው የሚገባውን ነገር ሊፈጽም የሚጠፋ ሰው ከአስረጅ በኋላ እንዲጠፋ ሕያው የሚኾንም ሰው ከአስረጅ በኋላ ሕያው እንዲኾን (ያለቀጠሮ አጋጠማችሁ)፡፡ አላህም በእርግጥ ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70