caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Anfaal፣ አንቀጽ 41

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 88 · 8:41

وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّمَا غَنِمْتُم مِّن شَىْءٍ فَأَنَّ لِلَّهِ خُمُسَهُۥ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينِ وَٱبْنِ ٱلسَّبِيلِ إِن كُنتُمْ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ وَمَآ أَنزَلْنَا عَلَىٰ عَبْدِنَا يَوْمَ ٱلْفُرْقَانِ يَوْمَ ٱلْتَقَى ٱلْجَمْعَانِ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy41.(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከማንኛዉም ነገር በጦርነት ከካሓዲያን የማረካችሁትም ሁሉ አንድ አምስተኛው ለአላህና ለመልዕክተኛው፤ ለነብዩ የዝምድና ባለቤቶች፤ ለየቲሞች፤ ለሚስኪኖች፤ ለመንገደኞችም የተገባ መሆኑን እወቁ:: በአላህና በዚያም እውነትና ውሸት በተለየበት ቀን ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙበት (በበድር) ቀን ባገልጋያችን ላይ ባወረድነውም የምታምኑ እንደ ሆናችሁ ይህንን እወቁ:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከማንኛውም ነገር በጦር (ከከሓዲዎች) የማረካችሁትን አንድ አምስተኛው ለአላህና ለመልክተኛው፣ (ለነቢዩ) የዝምድና ባለቤቶችም፣ ለየቲሞችም፣ ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኛም የተገባ መኾኑን ዕውቁ፣ በአላህና በዚያም እውነትና ውሸት በተለየበት ቀን ሁለቱ ጭፍሮች በተገናኙበት (በበድር) ቀን በባሪያችን ላይ ባወረድነው የምታምኑ እንደኾናችሁ (ይህንን ዕወቁ)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70