وَإِذَا رَأَيْتَ ٱلَّذِينَ يَخُوضُونَ فِىٓ ءَايَٰتِنَا فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا۟ فِى حَدِيثٍ غَيْرِهِۦ وَإِمَّا يُنسِيَنَّكَ ٱلشَّيْطَٰنُ فَلَا تَقْعُدْ بَعْدَ ٱلذِّكْرَىٰ مَعَ ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ አናቅጻችንን ለማስተባበል ወደ ክርክር የሚገቡትን ሰዎች በምታይ ጊዜ በሌላ ወሬ እስከሚገቡ ድረስ ተዋቸው:: ሰይጣንም መከልከልህን ቢያስረሳህና አብረሀቸው ሆነህ እንኳን ካስታወስክ በኋላ ከበደለኞች ሕዝቦች ጋር አትቀመጥ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያንም በአንቀጾቻችን የሚገቡትን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ሌላ በኾነ ወሬ እስከሚገቡ ድረስ ተዋቸው፡፡ ሰይጣንም (መከልከልህን) ቢያስረሳህ ከትውስታ በኋላ ከበደለኞች ሕዝቦች ጋር አትቀመጥ፡፡