caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 50

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:50

قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ إِنِّى مَلَكٌ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልላችሁም:: ሩቅ ሚስጥርንም አላውቅም:: መልዓክ ነኝም አልልም:: ወደ እኔ የሚወርድልኝን መልዕክት ብቻ እንጂ ሌላን አልከተልም።» በላቸው። «እውርና የሚያይ ይስተካከላሉን? አታስተነትኑምን!» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም አላውቅም፡፡ ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፡፡ ወደእኔ የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም» በላቸው፡፡ «ዕውርና የሚያይ ይስተካከላሉን አታስተነትኑምን» በላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70