هَلْ يَنظُرُونَ إِلَّآ أَن تَأْتِيَهُمُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَوْ يَأْتِىَ رَبُّكَ أَوْ يَأْتِىَ بَعْضُ ءَايَٰتِ رَبِّكَ يَوْمَ يَأْتِى بَعْضُ ءَايَٰتِ رَبِّكَ لَا يَنفَعُ نَفْسًا إِيمَٰنُهَا لَمْ تَكُنْ ءَامَنَتْ مِن قَبْلُ أَوْ كَسَبَتْ فِىٓ إِيمَٰنِهَا خَيْرًا قُلِ ٱنتَظِرُوٓا۟ إِنَّا مُنتَظِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy158. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን መላዕክት ልትመጣላቸው ወይንም ጌታህ ሊመጣ ወይም ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ ሊመጣ እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ የሚመጣበት ቀን ግን ከዚያ በፊት አማኝ ያልነበረች ነፍስ ሁሉ ወይም አምና በእምነቷ በጎ ያልሰራች ነፍስ ሁሉ እምነቷ (ጸጸቷ) አይጠቅማትም:: «ያን ቀን እናንተም ተጠባበቁ እኛም ተጠባባቂዎች ነን።» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqመላእክት ልትመጣላቸው ወይም ጌታህ ሊመጣ ወይም ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ ሊመጣ እንጂ ይጠባበቃሉን ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ በሚመጣ ቀን ከዚህ በፊት አማኝ ያልኾነችን ነፍስ እምነትዋ ወይም በእምነትዋ (ጊዜ) በጎ ያልሠራችን (ነፍስ ጸጸትዋ) አይጠቅማትም፡፡ ተጠባበቁ እኛ ተጠባባቂዎች ነንና በላቸው፡፡