caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 141

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:141

وَهُوَ ٱلَّذِىٓ أَنشَأَ جَنَّٰتٍ مَّعْرُوشَٰتٍ وَغَيْرَ مَعْرُوشَٰتٍ وَٱلنَّخْلَ وَٱلزَّرْعَ مُخْتَلِفًا أُكُلُهُۥ وَٱلزَّيْتُونَ وَٱلرُّمَّانَ مُتَشَٰبِهًا وَغَيْرَ مُتَشَٰبِهٍ كُلُوا۟ مِن ثَمَرِهِۦٓ إِذَآ أَثْمَرَ وَءَاتُوا۟ حَقَّهُۥ يَوْمَ حَصَادِهِۦ وَلَا تُسْرِفُوٓا۟ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلْمُسْرِفِينَ

Amharic Translation - Africa Academy141. አላህ ያ (በሀረጉ) ዳስ የሚያደርግላቸውንና ዳስ የማያደርግላቸውን አትክልቶች የፈጠረ ነው:: የተምርን ዛፍ፣ አዝመራን፣ ፍሬዎቹ የተለያዩ ሲሆኑ ወይራንና ሩማንንም ቅጠላቸው ተመሳሳይና ጣዕማቸው የማይመሳሰል ሲሆኑ ፈጠረ:: (ሰዎች ሆይ!) ባፈራ ጊዜም ከፍሬው ብሉ:: ባጨዳዉም ቀን ተገቢውን (ዘካ) ለተገቢው ስጡለት:: አታባክኑም:: አላህ አባካኞችን አይወድምና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእርሱም ያ ዳስ የሚደረግላቸውንና ዳስ የማይደረግላቸውን አትክልቶች የፈጠረ ነው፡፡ ዘምባባንም (የተምርን ዛፍ) አዝመራንም ፍሬዎቹ የተለያዩ ሲኾኑ ወይራንና ሩማንንም (ቅጠላቸው) ተመሳሳይና (ጣዕማቸው) የማይመሳሰል ሲኾኑ (ፈጠረ)፡፡ ባፈራ ጊዜ ከፍሬው ብሉ፡፡ በአጨዳውም ቀን ተገቢውን (ዘካ) ስጡ፡፡ አታባክኑም፡፡ እርሱ አባካኞችን አይወድምና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70