caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Noor፣ አንቀጽ 33

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 102 · 24:33

وَلْيَسْتَعْفِفِ ٱلَّذِينَ لَا يَجِدُونَ نِكَاحًا حَتَّىٰ يُغْنِيَهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦ وَٱلَّذِينَ يَبْتَغُونَ ٱلْكِتَٰبَ مِمَّا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُمْ فَكَاتِبُوهُمْ إِنْ عَلِمْتُمْ فِيهِمْ خَيْرًا وَءَاتُوهُم مِّن مَّالِ ٱللَّهِ ٱلَّذِىٓ ءَاتَىٰكُمْ وَلَا تُكْرِهُوا۟ فَتَيَٰتِكُمْ عَلَى ٱلْبِغَآءِ إِنْ أَرَدْنَ تَحَصُّنًا لِّتَبْتَغُوا۟ عَرَضَ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَمَن يُكْرِههُّنَّ فَإِنَّ ٱللَّهَ مِنۢ بَعْدِ إِكْرَٰهِهِنَّ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy33. እነዚያም የማግቢያን ጣጣ የማያገኙ ሰዎች አላህ ከችሮታው እስከሚያከብራቸው ድረስ ይጠብቁ። እነዚያንም እጆቻችሁ ከጨበጧቸው አገልጋዮች መካከል ገንዘብ ሰጥተው ነጻ ለመውጣት መጻጻፍን የሚፈልጉትን ከእነርሱ መልካም ነገርን ብታውቁ (ብታዩ) ተጻጻፏቸው:: አላህ ከሰጣችሁ ገንዘብም ስጧቸው:: ሴቶች ባሮቻችሁንም መጠበቅን ከፈለጉ የቅርቢቱን ህይወት ጥቅም ለመፈለግ ብላችሁ በዝሙት ተግባር ላይ አታስገድዷቸው:: የሚያስገድዳቸዉም ሰው አላህ ከመገደዳቸው በኋላ ለተገደዱት መሓሪና አዛኝ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያም የማግቢያን ጣጣ የማያገኙ አላህ ከችሮታው እስከሚያከብራቸው ድረስ ይጠበቁ፡፡ እነዚያንም እጆቻችሁ ከጨበጧቸው አገልጋዮች (ገንዘብ ሰጥተው ነጻ ለመውጣት) መጻጻፍን የሚፈልጉትን ከእነሱ መልካምን ነገር ብታውቁ ተጻጻፉዋቸው፡፡ ከአላህም ገንዘብ ከዚያ ከሰጣችሁ ስጧቸው፡፡ ሴቶች ባሮቻችሁንም መጥጠበቅን ቢፈልጉ የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም ለመፈለግ ብላችሁ በዝሙት ላይ አታስገድዱዋቸው፡፡ የሚያስገድዳቸውም ሰው አላህ ከመገደዳቸው በኋላ (ለተገደዱት) መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70