وَأَنكِحُوا۟ ٱلْأَيَٰمَىٰ مِنكُمْ وَٱلصَّٰلِحِينَ مِنْ عِبَادِكُمْ وَإِمَآئِكُمْ إِن يَكُونُوا۟ فُقَرَآءَ يُغْنِهِمُ ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy32. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከናንተ መካከል ትዳር የሌላቸውን ሰዎች አጋቡ:: ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የሆኑትን ክፍሎች አጋቡ:: ድሆች ከሆኑም አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል:: አላህ ስጦታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፡፡ ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የኾኑትን (አጋቡ)፡፡ ድኾች ቢኾኑ አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል፡፡ አላህም ስጦታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡