إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَهَاجَرُوا۟ وَجَٰهَدُوا۟ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ ءَاوَوا۟ وَّنَصَرُوٓا۟ أُو۟لَٰٓئِكَ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَآءُ بَعْضٍ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَلَمْ يُهَاجِرُوا۟ مَا لَكُم مِّن وَلَٰيَتِهِم مِّن شَىْءٍ حَتَّىٰ يُهَاجِرُوا۟ وَإِنِ ٱسْتَنصَرُوكُمْ فِى ٱلدِّينِ فَعَلَيْكُمُ ٱلنَّصْرُ إِلَّا عَلَىٰ قَوْمٍۭ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُم مِّيثَٰقٌ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy72. እነዚያ በአላህ አምነው ለእርሱም ሲሉ ከሀገራቸው የተሰደዱ በአላህ መንገድ ላይም በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የታገሉ እና እነዚያም ስደተኞቹን ያስጠጉና የረዱ ሰዎች እነዚያ ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: እነዚያ አምነውም ያልተሰደዱ ሰዎች ደግሞ ለአላህ ብለው እስከሚሰደዱ ድረስ ከእነርሱ ምንም ዝምድና የላችሁም:: በሃይማኖት እርዳታን ቢፈልጉባችሁ በእናንተና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ባላችሁ ሕዝቦች ላይ ካልሆነ በስተቀር በእናንተ ላይ እነርሱን መርዳት አለባችሁ:: አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ ያመኑና የተሰደዱ፡፡ በአላህም መንገድ ላይ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የታገሉ፡፡ እነዚያም (ስደተኞቹን) ያስጠጉና የረዱ፡፡ እነዚያ ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ እነዚያም ያመኑና ያልተሰደዱ እስከሚሰደዱ ድረስ ከነሱ ምንም ዝምድና የላችሁም፡፡ በሃይማኖትም እርዳታን ቢፈልጉባችሁ በእናንተና በነሱ መካከል ቃል ኪዳን ባላችሁ ሕዝቦች ላይ ካልኾነ በስተቀር በናንተ ላይ መርዳት አለባችሁ፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡