وَإِذْ يَمْكُرُ بِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِيُثْبِتُوكَ أَوْ يَقْتُلُوكَ أَوْ يُخْرِجُوكَ وَيَمْكُرُونَ وَيَمْكُرُ ٱللَّهُ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም ከመካ ሊያስወጡህ ባንተ ላይ ባሴሩብህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ያሴራሉም:: አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል:: አላህ ግን ከሴረኞቹ ሁሉ በላይ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም (ከመካ) ሊያወጡህ ባንተ ላይ በመከሩብህ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ይመክራሉም አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል፡፡ አላህም ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው፡፡