إِن تَسْتَفْتِحُوا۟ فَقَدْ جَآءَكُمُ ٱلْفَتْحُ وَإِن تَنتَهُوا۟ فَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ وَإِن تَعُودُوا۟ نَعُدْ وَلَن تُغْنِىَ عَنكُمْ فِئَتُكُمْ شَيْـًٔا وَلَوْ كَثُرَتْ وَأَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلْمُؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy19. (ከሓዲያን ሆይ!) ፍትሕን ብትጠይቁ ፍትሁ በእርግጥ መጥቶላችኋል:: ክሕደትና መዋጋታችሁን ብትከለከሉም እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው:: ወደ መጋደል ብትመለሱም እንመለሳለን:: ሰራዊታችሁ ብትበዛም እንኳ ለእናንተ ምንም አትጠቅማችሁም:: አላህ ሁልጊዜም ከትክክለኛ አማኞች ጋር ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqፍትሕን (ፍርድን) ብትጠይቁ ፍትሑ በእርግጥ መጥቶላችኋል፡፡ (ክህደትንና መዋጋትን) ብትከለከሉም እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ (ወደ መጋደል) ብትመለሱም እንመለሳለን፡፡ ሰራዊታችሁም ብትበዛም እንኳ ከናንተ ምንም አትጠቅማችሁም፡፡ አላህም ከምእምናን ጋር ነው፡፡