caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 25

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:25

وَمِنْهُم مَّن يَسْتَمِعُ إِلَيْكَ وَجَعَلْنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ أَكِنَّةً أَن يَفْقَهُوهُ وَفِىٓ ءَاذَانِهِمْ وَقْرًا وَإِن يَرَوْا۟ كُلَّ ءَايَةٍ لَّا يُؤْمِنُوا۟ بِهَا حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوكَ يُجَٰدِلُونَكَ يَقُولُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِنْ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلْأَوَّلِينَ

Amharic Translation - Africa Academy25. ከእነርሱ መካከል ወደ አንተ የሚያዳምጥ ሰው አለ:: በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሽፋኖችን፤ በጆሮዎቻቸዉም ላይ እንዳይሰሙት ድንቁርናን አደረግን:: ተዐምርን ሁሉ እንኳን ቢያዩ በእርሷ አያምኑም:: ወደ አንተ በመጡ ጊዜ የሚከራከሩህ ሆነው እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች «ይህ ቁርኣን የቀድሞዎቹ ሰዎች ጹሑፍ ተረቶች ስብስብ እንጂ ሌላ አይደለም።» ይላሉ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከእነርሱም ወደ አንተ የሚያዳምጥ ሰው አልለ፡፡ በልቦቻቸውም ላይ እንዳያውቁት ሺፋኖችን በጆሮዎቻቸውም ላይ ድንቁርናን አደረግን፡፡ ተዓምርንም ሁሉ ቢያዩ በርሷ አያምኑም፡፡ በመጡህም ጊዜ የሚከራከሩህ ሲኾኑ እነዚያ የካዱት «ይህ (ቁርኣን) የቀድሞዎቹ ሰዎች ጽሑፍ ተረቶች እንጅ ሌላ አይደለም» ይላሉ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70