caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 19

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:19

قُلْ أَىُّ شَىْءٍ أَكْبَرُ شَهَٰدَةً قُلِ ٱللَّهُ شَهِيدٌۢ بَيْنِى وَبَيْنَكُمْ وَأُوحِىَ إِلَىَّ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانُ لِأُنذِرَكُم بِهِۦ وَمَنۢ بَلَغَ أَئِنَّكُمْ لَتَشْهَدُونَ أَنَّ مَعَ ٱللَّهِ ءَالِهَةً أُخْرَىٰ قُل لَّآ أَشْهَدُ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌ وَإِنَّنِى بَرِىٓءٌ مِّمَّا تُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከምስክርነት ሁሉ ይበልጥ ታላቁ የትኛው ነው?» በላቸው። «አላህ፤ በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ ነው። ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውንም ሁሉ ላስፈራራበት ወደ እኔ ተወረደ:: ከአላህ ጋር ሌሎች አማልክት መኖራቸውን እናንተ ትመሰክራላቸሁን?» በላቸው:: «እኔ ግን ፈጽሞ በዚህ አልመሰክርም።» በላቸው:: «እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እኔም በአላህ ከምታጋሩት ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«በምስክርነት ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ማነው» በላቸው፡፡ (ሌላ መልስ የለምና) «አላህ ነው፡፡ በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ ነው፡፡ ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውን ሰው ሁሉ በርሱ ላስፈራራበት ወደኔ ተወረደ፡፡ ከአላህ ጋር ሌሎች አማልክት መኖራቸውን እናንተ ትመሰክራላችሁን؟» በላቸው፡፡ «እኔ አልመሰክርም» በላቸው፡፡ «እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70