قُل لَّآ أَجِدُ فِى مَآ أُوحِىَ إِلَىَّ مُحَرَّمًا عَلَىٰ طَاعِمٍ يَطْعَمُهُۥٓ إِلَّآ أَن يَكُونَ مَيْتَةً أَوْ دَمًا مَّسْفُوحًا أَوْ لَحْمَ خِنزِيرٍ فَإِنَّهُۥ رِجْسٌ أَوْ فِسْقًا أُهِلَّ لِغَيْرِ ٱللَّهِ بِهِۦ فَمَنِ ٱضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ رَبَّكَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy145. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ወደ እኔ በተወረደው ቁርኣን ውስጥ በክት ወይም የፈሰሰ ደም፤ ወይም የአሳማ ስጋ እርሱ እርኩስ ነውና፤ ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልሆነ በስተቀር ተመጋቢ ላይ እርም የሆነ ነገር አላገኝም። አመጸኛና ወሰን ያለፈ ሳይሆን የተገደደ ሰው ከተወሱት ነገሮች ነፍስን የማዳን ያህል ቢበላ ኃጢአት የለበትም:: ጌታህ መሀሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው፡- «ወደእኔ በተወረደው ውስጥ በክት ወይም ፈሳሽ ደም ወይም የአሳማ ስጋ እርሱ ርኩስ ነውና ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልኾነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የኾነን ነገር አላገኝም፡፡ አመጸኛና ወሰን ያለፈ ሳይኾንም የተገደደ ሰው (ከተወሱት ቢበላ ኃጢአት የለበትም)፡፡ ጌታህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡»