caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Noor፣ አንቀጽ 62

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 102 · 24:62

إِنَّمَا ٱلْمُؤْمِنُونَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَإِذَا كَانُوا۟ مَعَهُۥ عَلَىٰٓ أَمْرٍ جَامِعٍ لَّمْ يَذْهَبُوا۟ حَتَّىٰ يَسْتَـْٔذِنُوهُ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسْتَـْٔذِنُونَكَ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ فَإِذَا ٱسْتَـْٔذَنُوكَ لِبَعْضِ شَأْنِهِمْ فَأْذَن لِّمَن شِئْتَ مِنْهُمْ وَٱسْتَغْفِرْ لَهُمُ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy62. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትክክለኛ አማኞች ማለት እነዚያ በአላህና በመልዕክተኛው ያመኑት:: ከመልዕክተኛው ጋር በሚሰበሰብ ጉዳይ ላይ በሆኑ ጊዜ እስከሚያስፈቅዱት ድረስ የማይሄዱት ብቻ ናቸው:: እነዚያ የሚያስፈቅዱህ እርሱ እነዚያ በትክክል በአላህና በመልዕክተኛው የሚያምኑት ናቸው:: ለግል ጉዳያቸዉም ፈቃድ በጠየቁህ ጊዜ ከእነርሱ ላሻኸው ሰው ፍቀድለት:: ለእነርሱም ከአላህ ምህረትን ለምንላቸው:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqምእመናን ማለት እነዚያ በአላህና በመልክተኛው ያመኑት፤ ከእርሱ ጋር በሚሰበሰብ ጉዳይ ላይ በኾኑ ጊዜ እስከሚያስፈቅዱ ድረስ የማይኼዱት ብቻ ናቸው፡፡ እነዚያ የሚያስፈቅዱህ እነርሱ እነዚያ በአላህና በመልክተኛው የሚያምኑት ናቸው፡፡ ለግል ጉዳያቸውም ፈቃድ በጠየቁህ ጊዜ ከእነሱ ለሻኸው ሰው ፍቀድለት፡፡ ለእነሱም አላህን ምሕረትን ለምንላቸው አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70