caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Noor፣ አንቀጽ 61

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 102 · 24:61

لَّيْسَ عَلَى ٱلْأَعْمَىٰ حَرَجٌ وَلَا عَلَى ٱلْأَعْرَجِ حَرَجٌ وَلَا عَلَى ٱلْمَرِيضِ حَرَجٌ وَلَا عَلَىٰٓ أَنفُسِكُمْ أَن تَأْكُلُوا۟ مِنۢ بُيُوتِكُمْ أَوْ بُيُوتِ ءَابَآئِكُمْ أَوْ بُيُوتِ أُمَّهَٰتِكُمْ أَوْ بُيُوتِ إِخْوَٰنِكُمْ أَوْ بُيُوتِ أَخَوَٰتِكُمْ أَوْ بُيُوتِ أَعْمَٰمِكُمْ أَوْ بُيُوتِ عَمَّٰتِكُمْ أَوْ بُيُوتِ أَخْوَٰلِكُمْ أَوْ بُيُوتِ خَٰلَٰتِكُمْ أَوْ مَا مَلَكْتُم مَّفَاتِحَهُۥٓ أَوْ صَدِيقِكُمْ لَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ أَن تَأْكُلُوا۟ جَمِيعًا أَوْ أَشْتَاتًا فَإِذَا دَخَلْتُم بُيُوتًا فَسَلِّمُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِكُمْ تَحِيَّةً مِّنْ عِندِ ٱللَّهِ مُبَٰرَكَةً طَيِّبَةً كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلْـَٔايَٰتِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy61. (ከሰዎች ጋር በመብላት) በዕውር (አይነስውር) ላይ ኃጢአት የለበትም:: በአንካሳም ላይ ኃጢአት የለበትም:: በበሽተኛም ላይ ኃጢአት የለበትም:: በነፍሶቻችሁም ላይ ከቤቶቻችሁ ወይም ከአባቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከእናቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከውድሞቻችሁ ቤቶች ወይም ከእህቶቻችሁ ቤቶች፤ ወይም ከአባት ወንድሞች አጎቶቻችሁ ቤቶች፤ ወይም ከአባት እህቶች አክስቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከእናት ወንድሞች የሹሞቻችሁ ቤቶች፤ ወይም ከእናት እህቶች የሜዎቻችሁ ቤቶች ወይም መክፈቻዎችን ከያዛችሁት ቤት ወይም ከወዳጃችሁ ቤት ብትበሉ ኃጢአት የለባችሁም:: ተሰብስባችሁ ወይም ተለያይታችሁ ብትበሉ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ ከአላህ ዘንድ የሆነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ:: ልክ እንደዚህ አላህ አናቅጽን ለእናንተ ያብራራል፤ ልታውቁ ይከጅላልና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ከሰዎች ጋር በመብላት) በዕውር ላይ ኀጢአት የለበትም፡፡ በአንካሳም ላይ ኀጢአት የለበትም፡፡ በበሽተኛም ላይ ኀጢአት የለበትም፡፡ በነፍሶቻችሁም ላይ ከቤቶቻችሁ ወይም ከአባቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከእናቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከወንድሞቻችሁ ቤቶች ወይም ከእኅቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከአጎቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከአክስቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከየሹሞቻችሁ ቤቶች ወይም ከየሹሜዎቻችሁ ቤቶች ወይም መክፈቻዎቹን ከያዛችሁት ቤት ወይም ከወዳጃችሁ ቤት (ብትበሉ) ኀጢአት የለባችሁም፡፡ ተሰብስባችሁ ወይም ተለያይታችሁ ብትበሉ በእናንተ ላይ ኀጢአት የለባችሁም፡፡ ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ፤ ከአላህ ዘንድ የኾነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ፡፡ እንደዚሁ አላህ አንቀጾችን ለእናንተ ያብራራል፡፡ ልታውቁ ይከጀላልና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70