يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لِيَسْتَـْٔذِنكُمُ ٱلَّذِينَ مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُمْ وَٱلَّذِينَ لَمْ يَبْلُغُوا۟ ٱلْحُلُمَ مِنكُمْ ثَلَٰثَ مَرَّٰتٍ مِّن قَبْلِ صَلَوٰةِ ٱلْفَجْرِ وَحِينَ تَضَعُونَ ثِيَابَكُم مِّنَ ٱلظَّهِيرَةِ وَمِنۢ بَعْدِ صَلَوٰةِ ٱلْعِشَآءِ ثَلَٰثُ عَوْرَٰتٍ لَّكُمْ لَيْسَ عَلَيْكُمْ وَلَا عَلَيْهِمْ جُنَاحٌۢ بَعْدَهُنَّ طَوَّٰفُونَ عَلَيْكُم بَعْضُكُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلْـَٔايَٰتِ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy58. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው ባሮች እነዚያም ከናንተ መካከል ለአካለ መጠን ያልደረሱት (ህፃናት) በሶስት ጊዜ: ከጎህ ስግደት በፊት፤ በቀትር ልብሶቻችሁን በምታወልቁበት ጊዜና ከምሽት ስግደትም በኋላ ወደ እናንተ ለመግባት ሲፈልጉ ያስፈቅዷችሁ:: እነዚህ የእናንተ ሶስት የሐፍረተ ገላ መግለጫ ጊዜያቶች ናቸውና:: ከእነዚህ በኋላ ግን በእናንተም ሆነ በነሱ ላይ (ያለፈቃድ በመግባት) ኃጢአት የለም:: እናንተን ለማገልገል በዙሪያችሁ ዟሪዎች ናቸውና:: ከፊላችሁ በከፊሉ ላይ ዟሪ ነውና፤ ልክ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ ህግጋቱን ይገልጽላችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው (ባሮች) እነዚያም ከእናንተ ለአካላ መጠን ያልደረሱት ከጎህ ስግደት በፊት፣ በቀትርም ልብሶቻችሁን በምታወልቁ ጊዜ ከምሽት ስግደትም በኋላ ሦስት ጊዜያት (ለመግባት ሲፈልጉ) ያስፈቅዷችሁ፡፡ (እነዚህ) ለእናንተ የኾኑ ሦስት የሐፍረተ ገላ መገለጫ ጊዜያቶች ናቸውና፡፡ ከእነዚህ በኋላ በእናንተም በእነርሱም ላይ (ያለፈቃድ በመግባት) ኀጢአት የለም፡፡ በእናንተ ላይ (ለማገልገል) ዙዋሪዎች ናቸውና፡፡ ከፊላችሁ በከፊሉ ላይ ዙዋሪ ነው፡፡ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ ሕግጋትን ይገልጽላችኋል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡