caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Anfaal፣ አንቀጽ 48

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 88 · 8:48

وَإِذْ زَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيْطَٰنُ أَعْمَٰلَهُمْ وَقَالَ لَا غَالِبَ لَكُمُ ٱلْيَوْمَ مِنَ ٱلنَّاسِ وَإِنِّى جَارٌ لَّكُمْ فَلَمَّا تَرَآءَتِ ٱلْفِئَتَانِ نَكَصَ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ وَقَالَ إِنِّى بَرِىٓءٌ مِّنكُمْ إِنِّىٓ أَرَىٰ مَا لَا تَرَوْنَ إِنِّىٓ أَخَافُ ٱللَّهَ وَٱللَّهُ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

Amharic Translation - Africa Academy48. ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ባሳመረላቸውና «ዛሬ ለእናንተ ከሰዎች አሸናፊ የላችሁም:: እኔም ለእናንተ ረዳት ነኝ።» ባለ ጊዜም (የሆነውን አስታውስ):: ሁለቱ ቡድኖችም በተያዩ ጊዜ ወደኋላው አፈገፈገ:: «እኔ ከናንተ ንጹህ ነኝ:: እኔ እናንተ የማታዩትን አያለሁ:: እኔ አላህን እፈራለሁ:: አላህም ቅጣተ ብርቱ ነው።» አላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ባሳመረላቸውና «ዛሬ ለእናንተ ከሰዎች አሸናፊ የላችሁም እኔም ለእናንተ ረዳት ነኝ» ባለ ጊዜም (አስታውስ)፡፡ ሁለቱ ጭፍሮችም በተያዩ ጊዜ፤ ወደኋላው አፈገፈገ፡፡ «እኔ ከናንተ ንጹህ ነኝ፡፡ እኔ እናንተ የማታዩትን አያለሁ፡፡ እኔ አላህን እፈራለሁ፡፡ አላህም ቅጣተ ብርቱ ነው» አላቸውም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70