بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْأَنفَالِ قُلِ ٱلْأَنفَالُ لِلَّهِ وَٱلرَّسُولِ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَصْلِحُوا۟ ذَاتَ بَيْنِكُمْ وَأَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy1.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጦርነት ከተማረኩ ገንዘቦች ይጠይቁሃል። «በጦርነት የተዘረፉ ገንዘቦች የአላህና የመልዕክተኛው ናቸው:: ስለዚህ አላህን ፍሩ:: በመካከላችሁ ያለውንም ሁኔታ አሳምሩ:: ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከጦር ዘረፋ ገንዘቦች ይጠይቁሃል፡፡ «የዘረፋ ገንዘቦች የአላህና የመልክተኛው ናቸው፡፡» ስለዚህ አላህን ፍሩ፡፡ በመካከላችሁ ያለችውንም ኹኔታ አሳምሩ፡፡ አማኞችም እንደኾናችሁ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ በላቸው፡፡