يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا جَآءَكُمُ ٱلْمُؤْمِنَٰتُ مُهَٰجِرَٰتٍ فَٱمْتَحِنُوهُنَّ ٱللَّهُ أَعْلَمُ بِإِيمَٰنِهِنَّ فَإِنْ عَلِمْتُمُوهُنَّ مُؤْمِنَٰتٍ فَلَا تَرْجِعُوهُنَّ إِلَى ٱلْكُفَّارِ لَا هُنَّ حِلٌّ لَّهُمْ وَلَا هُمْ يَحِلُّونَ لَهُنَّ وَءَاتُوهُم مَّآ أَنفَقُوا۟ وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ أَن تَنكِحُوهُنَّ إِذَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ وَلَا تُمْسِكُوا۟ بِعِصَمِ ٱلْكَوَافِرِ وَسْـَٔلُوا۟ مَآ أَنفَقْتُمْ وَلْيَسْـَٔلُوا۟ مَآ أَنفَقُوا۟ ذَٰلِكُمْ حُكْمُ ٱللَّهِ يَحْكُمُ بَيْنَكُمْ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy10. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሴት ምዕመናት ስደተኞች ሆነው ወደ እናንተ በሚመጡበት ጊዜ (ለሀይማኖት ሲሉ መሰደዳቸውን) ፈትኗቸው:: አላህ በእምነታቸው ከናንተ ይልቅ አዋቂ ነው:: ትክክለኛ አማኞችም መሆናቸውን ብታውቁ ወደ ከሓዲያን ባሎቻቸው አትመልሷቸው:: እነርሱ ሙስሊም ሴቶች ለከሓዲ ወንዶች አይፈቀዱምና:: ከሓዲያን ወንዶችም ለአማኝ ሴቶች የተፈቀዱ አይደሉምና:: ያወጡትንም ገንዘብ መህሩን ስጧቸው:: መህራቸውንም ከሰጣችኋቸው ብታገቧቸው ኃጢአት የለባችሁም :: የከሓዲያንንም ሴቶች የጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ:: ሆኖም እናንተ ያወጣችሁትን ገንዘብ ጠይቁ :: እነርሱም ያወጡትን ይጠይቁ:: ይህ የአላህ ፍርድ ነውና:: በመካከላችሁም ይፈርዳል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእላንተ ያመናችሁ ሆይ! ምእምናት ስደተኞች ኾነው በመጧችሁ ጊዜ (ለሃይማኖት መሰደዳቸውን) ፈትኑዋቸው፡፡ አላህ በእምነታቸው ይበልጥ ዐዋቂ ነው፡፡ አማኞችም መኾናቸውን ብትውቁ ወደ ከሓዲዎቹ አትመልሱዋቸው፡፡ እነርሱ (ሴቶቹ) ለእነርሱ የተፈቀዱ አይደሉምና፡፡ እነርሱም (ወንዶቹ) ለእነርሱ አይፈቀዱምና፡፡ ያወጡትንም ገንዘብ ስጧቸው፡፡ መህራቸውንም በሰጣችኋቸው ጊዜ ብታገቡዋቸው በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም፡፡ የከሓዲዎቹንም ሴቶች የጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ፤ ያወጣችሁትንም ገንዘብ ጠይቁ፡፡ ያወጡትንም ይጠይቁ፡፡ ይህ የአላህ ፍርድ ነው፡፡ በመካከላችሁ ይፈርዳል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡