caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 54

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:54

وَإِذَا جَآءَكَ ٱلَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِـَٔايَٰتِنَا فَقُلْ سَلَٰمٌ عَلَيْكُمْ كَتَبَ رَبُّكُمْ عَلَىٰ نَفْسِهِ ٱلرَّحْمَةَ أَنَّهُۥ مَنْ عَمِلَ مِنكُمْ سُوٓءًۢا بِجَهَٰلَةٍ ثُمَّ تَابَ مِنۢ بَعْدِهِۦ وَأَصْلَحَ فَأَنَّهُۥ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በተዐምራታችን የሚያምኑት ሰዎች ሁሉ ወደ አንተ በመጡ ጊዜ «ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን:: ጌታችን በራሱ ላይ እዝነትን ፃፈ:: እነሆ ከናንተ ውስጥ ስህተትን ስራ የሰራና ከዚያ ተጸጽቶ ወዲያውኑ ስራውን ላሳመረ እርሱ (አላህ) መሀሪና አዛኝ ነው።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያም በተአምራታችን የሚያምኑት (ወደ አንተ) በመጡ ጊዜ «ሰላም በእናንተ ላይ ይኹን፡፡ ጌታችሁ በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡ እነሆ ከእናንተ ውስጥ በስሕተት ክፉን ሥራ የሠራ ሰው ከዚያም ከእርሱ በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ እርሱ (አላህ) መሓሪ አዛኝ ነው» በላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70