caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 31

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:31

قَدْ خَسِرَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِلِقَآءِ ٱللَّهِ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَتْهُمُ ٱلسَّاعَةُ بَغْتَةً قَالُوا۟ يَٰحَسْرَتَنَا عَلَىٰ مَا فَرَّطْنَا فِيهَا وَهُمْ يَحْمِلُونَ أَوْزَارَهُمْ عَلَىٰ ظُهُورِهِمْ أَلَا سَآءَ مَا يَزِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy31. እነዚያ ከአላህ ጋር መገናኘትን ያስተባበሉ ሁሉ በእርግጥ ከሰሩ:: ስዓቲቱም በድንገት በመጣችባቸው ጊዜ እነርሱ ኃጢአቶቻቸውን በጀርባዎቻቸው ላይ የሚሸከሙ ሲሆኑ «በምድረ ዓለም ባጓደልነው ነገር ላይ ዋ ጥፋታችን!» ይላሉ። አዋጅ ያ የሚሸከሙት ነገር ምንኛ ከፋ!
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉ በእርግጥ ከሰሩ፡፡ ሰዓቲቱም በድንገት በመጣቻቸው ጊዜ እነሱ ኃጢኣቶቻቸውን በጀርባዎቻቸው ላይ የሚሸከሙ ሲኾኑ «በርሷ (በምድረ ዓለም) ባጓደልነው ነገር ላይ ዋ ቁጪታችን» ይላሉ፡፡ ንቁ! የሚሸከሙት ነገር ከፋ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70