يَٰمَعْشَرَ ٱلْجِنِّ وَٱلْإِنسِ أَلَمْ يَأْتِكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ ءَايَٰتِى وَيُنذِرُونَكُمْ لِقَآءَ يَوْمِكُمْ هَٰذَا قَالُوا۟ شَهِدْنَا عَلَىٰٓ أَنفُسِنَا وَغَرَّتْهُمُ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا وَشَهِدُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا۟ كَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy130. «የአጋንትና የሰዎች ቡድኖች ሆይ! አንቀፆቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን ቅጣት ማግኘትን የሚያስፈራሯችሁ ከናንተው የሆኑ መልዕክተኞች አልመጡላችሁም ነበርን?» ይባላሉ:: «በነፍሶቻችን ላይ መሰከርን።» ይላሉ። የዱንያ ህይወት አታለለቻቸው። በነፍሶቻቸው ላይ እነርሱ ከሓዲያን የነበሩ መሆናቸውንም በራሳቸው መሰከሩ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየጋኔንና የሰዎች ጭፍሮች ሆይ!፡- «አንቀጾቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን (ቅጣት) ማግኘትን የሚያስፈራሩዋችሁ ከእናንተው የኾኑ መልክተኞች አልመጧችሁምን» (ይባላሉ)፡፡ «በነፍሶቻችን ላይ መሰከርን፤ (መጥተውልናል)» ይላሉ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት አታለለቻቸው፡፡ በነፍሶቻቸውም ላይ እነርሱ ከሓዲዎች የነበሩ መኾናቸውን መሰከሩ፡፡