قُل لِّمَن مَّا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ قُل لِّلَّهِ كَتَبَ عَلَىٰ نَفْسِهِ ٱلرَّحْمَةَ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ فَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የማን ነው?» በላቸውም: «የአላህ ብቻ ነው። አላህ በራሱ ላይ እዝነትን ፃፈ:: በዚያ ጥርጥር በሌለበት በትንሳኤ ቀን ይሰበስባችኋል:: እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ማለት እነርሱው ናቸው። እናም አያምኑም።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የማን ነው» በላቸው፡፡ (ሌላ መልስ የለምና) «የአላህ ነው» በል፡፡ «በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡ በትንሣኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲኾን በእርግጥ ይሰበስባችኋል፡፡ እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፤ እነርሱም አያምኑም፡፡