فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ شَهْرَيْنِ مُتَتَابِعَيْنِ مِن قَبْلِ أَن يَتَمَآسَّا فَمَن لَّمْ يَسْتَطِعْ فَإِطْعَامُ سِتِّينَ مِسْكِينًا ذَٰلِكَ لِتُؤْمِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَتِلْكَ حُدُودُ ٱللَّهِ وَلِلْكَٰفِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy4. ይህን ላላገኘም ሰው ከመነካካታቸው በፊት ሁለት ተከታታይ ወሮችን መፆም አለበት:: ይህን ላልቻለም ሰው ስልሳ ድሆችን ማብላት አለበት:: ይህ በአላህና በመልዕክተኛው እንድታምኑ ነው:: እነኚህ ህግጋት የአላህ ህግጋት ናቸው:: (እናም አትተላለፏቸው::) ለከሓዲያንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqያላገኘም ሰው ከመነካከታቸው በፊት ሁለት የተከታተሉ ወሮችን መጾም አለበት፡፡ ያልቻለም ሰው ስድሳ ድኾችን ማብላት (አለበት)፡፡ ይህ በአላህና በመልክተኛው እንድታምኑ ነው፡፡ ይህችም የአላህ ሕግጋት ናት፡፡ ለከሓዲዎችም አሳማሚ ቅጣት አልላቸው፡፡