إِلَيْهِ يُرَدُّ عِلْمُ ٱلسَّاعَةِ وَمَا تَخْرُجُ مِن ثَمَرَٰتٍ مِّنْ أَكْمَامِهَا وَمَا تَحْمِلُ مِنْ أُنثَىٰ وَلَا تَضَعُ إِلَّا بِعِلْمِهِۦ وَيَوْمَ يُنَادِيهِمْ أَيْنَ شُرَكَآءِى قَالُوٓا۟ ءَاذَنَّٰكَ مَا مِنَّا مِن شَهِيدٍ
Amharic Translation - Africa Academy47. የትንሳኤ መከሰቻ ሰዐቱን ማወቅ ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳል:: ከፍሬዎችም ከሽፋኖቻቸው አይወጡም ከሴትም አንዲትም አታረግዝም፤ አትወልድምም በእውቀቱ ቢሆን እንጂ:: «ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» በማለት በሚጠራቸው ቀንም ከእኛ ውስጥ («ተጋሪ አለህ» ብሎ) ምንም መስካሪ አለመኖሩን አምነናል» ይላሉ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqጊዜይቱን ማወቅ ወደእርሱ ይመለሳል ከፍሬዎችም ከሽፋኖቻቸው አይወጡም፤ ከሴትም አንዲትም አታረግዝም፣ አትወልድምም በዕውቀቱ ቢኾን እንጅ፡፡ «ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» በማለት በሚጠራቸው ቀንም «ከእኛ ውስጥ (ባላንጣ አልለ ብሎ) ምንም መስካሪ አለመኖሩን አስታወቅንህ» ይላሉ፡፡