وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنكُمْ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَيَسْتَخْلِفَنَّهُمْ فِى ٱلْأَرْضِ كَمَا ٱسْتَخْلَفَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ وَلَيُمَكِّنَنَّ لَهُمْ دِينَهُمُ ٱلَّذِى ٱرْتَضَىٰ لَهُمْ وَلَيُبَدِّلَنَّهُم مِّنۢ بَعْدِ خَوْفِهِمْ أَمْنًا يَعْبُدُونَنِى لَا يُشْرِكُونَ بِى شَيْـًٔا وَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy55. አላህ እነዚያን ከናንተ መካከል በትክክል ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን እንደተካቸው ሁሉ በምድር ላይ በእርግጥ ሊተካቸው፤ ለእነርሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፤ ከፍርሃታቸዉም በኋላ ደህናነትን ሊለውጥላቸው የተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል:: በእኔ ምንንም የማያጋሩ ሆነው ሊገዙኝ ነው፤ ከዚያም በኋላ በሱ የካዱ ሰዎች እነዚያ አመጸኞች ማለት እነርሱ ብቻ ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ እነዚያን ከእናንተ ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን እነዚያን ከእነሱ በፊት የነበሩትን እንደተካ በምድር ለይ በእርግጥ ሊተካቸው፣ ለእነሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፣ ከፍርሃታቸውም በኋላ ጸጥታን ሊለውጥላቸው ተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል፡፡ በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ይግገዙኛል፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡