إِنْ أَحْسَنتُمْ أَحْسَنتُمْ لِأَنفُسِكُمْ وَإِنْ أَسَأْتُمْ فَلَهَا فَإِذَا جَآءَ وَعْدُ ٱلْـَٔاخِرَةِ لِيَسُـۥٓـُٔوا۟ وُجُوهَكُمْ وَلِيَدْخُلُوا۟ ٱلْمَسْجِدَ كَمَا دَخَلُوهُ أَوَّلَ مَرَّةٍ وَلِيُتَبِّرُوا۟ مَا عَلَوْا۟ تَتْبِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy7. መልካምን ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ:: መጥፎንም ብትሠሩ በነፍሶቻችሁ ላይ ነው:: የኋለኛይቱ ጥፋት ቀጠሮ በደረሰ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ፤ መስጊዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡቡት ሊገቡ፤ ያሸነፉትንም ሁሉ ፈጽመው ማጥፋትን እንዲያጠፉ እንልካቸዋለን::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqመልካም ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ፡፡ መጥፎንም ብትሠሩ በነርሱ (በነፍሶቻችሁ) ላይ ነው፤ (አልን)፡፡ የኋለኛይቱም (ጊዜ) ቀጠሮ በመጣ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ፣ መስጊዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡት ሊገቡ፣ ያሸነፉትንም ሁሉ (ፈጽመው) ማጥፋትን እንዲያጠፉ (እንልካቸዋልን)፡፡