وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوٓا۟ إِلَّآ إِيَّاهُ وَبِٱلْوَٰلِدَيْنِ إِحْسَٰنًا إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِندَكَ ٱلْكِبَرَ أَحَدُهُمَآ أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَآ أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا
Amharic Translation - Africa Academy23. (የሰው ልጅ ሆይ!) ጌታህ እንዲህ ሲል አዘዘ:: እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ ለወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፤ ባንተ ዘንድ ሆነው ከወላጆችህ አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ «ኡፍ!» እንኳን አትበላቸው:: አትገላምጣቸዉም:: ለእነርሱም መልካምን ቃል ብቻ ተናገራቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፡፡ በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ አትበላቸው፡፡ አትገላምጣቸውም፡፡ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው፡፡