caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Anfaal፣ አንቀጽ 17

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 88 · 8:17

فَلَمْ تَقْتُلُوهُمْ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ قَتَلَهُمْ وَمَا رَمَيْتَ إِذْ رَمَيْتَ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ رَمَىٰ وَلِيُبْلِىَ ٱلْمُؤْمِنِينَ مِنْهُ بَلَآءً حَسَنًا إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy17. እናንተ አልገደላችኋቸዉም:: ግን አላህ ገደላቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጭብጥን አፈር በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም:: ግን አላህ ወረወረ። አማኞችን ሁሉ ከእርሱ የሆነን መልካም ፈተናን ለመፈተን ይህንን አደረገ። አላህም ሁሉን ሰሚ፤ ሁሉንም አዋቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአልገደላችኋቸውም ግን አላህ ገደላቸው፡፡ (ጭብጥን ዐፈር) በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም፡፡ ግን አላህ ወረወረ (ወደ ዓይኖቻቸው አደረሰው)፡፡ ለአማኞችም ከርሱ የኾነን መልካም ጸጋ ለመስጠት (ይህን አደረገ)፡፡ አላህ ሰሚ ዐዋቂ ነውና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70