إِذْ يُوحِى رَبُّكَ إِلَى ٱلْمَلَٰٓئِكَةِ أَنِّى مَعَكُمْ فَثَبِّتُوا۟ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ سَأُلْقِى فِى قُلُوبِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱلرُّعْبَ فَٱضْرِبُوا۟ فَوْقَ ٱلْأَعْنَاقِ وَٱضْرِبُوا۟ مِنْهُمْ كُلَّ بَنَانٍ
Amharic Translation - Africa Academy12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ወደ መላዕክቱ «እኔ በእርዳታዬ ከናንተ ጋር ነኝና እነዚያን በእኔ ያመኑትን ሰዎች አጽናኑ:: በእነዚያ በአላህ በካዱት ልቦች ውስጥ ደግሞ ፍርሀትን እጥላለሁ:: ከአንገቶችም በላይ እራሶችን ምቱ:: ከእነርሱም የቅርንጫፎችን መለያ ( አትቆች) ሁሉ ምቱ።» ሲል ያወረደውን አስታውስ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqጌታህ ወደ መላእክቱ «እኔ (በእርዳታዬ) ከእናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ፡፡ በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ፡፡ ከአንገቶችም በላይ (ራሶችን) ምቱ፡፡ ከእነሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ ሁሉ ምቱ፡፡» ሲል ያወረደውን (አስታውስ)፡፡