caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Mumtahana፣ አንቀጽ 4

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 91 · 60:4

قَدْ كَانَتْ لَكُمْ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ فِىٓ إِبْرَٰهِيمَ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥٓ إِذْ قَالُوا۟ لِقَوْمِهِمْ إِنَّا بُرَءَٰٓؤُا۟ مِنكُمْ وَمِمَّا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ كَفَرْنَا بِكُمْ وَبَدَا بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمُ ٱلْعَدَٰوَةُ وَٱلْبَغْضَآءُ أَبَدًا حَتَّىٰ تُؤْمِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَحْدَهُۥٓ إِلَّا قَوْلَ إِبْرَٰهِيمَ لِأَبِيهِ لَأَسْتَغْفِرَنَّ لَكَ وَمَآ أَمْلِكُ لَكَ مِنَ ٱللَّهِ مِن شَىْءٍ رَّبَّنَا عَلَيْكَ تَوَكَّلْنَا وَإِلَيْكَ أَنَبْنَا وَإِلَيْكَ ٱلْمَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy4. ኢብራሂምና እነዚያ ከእርሱ ጋር አብረው የነበሩት አማኞች ለእናንተ መልካም አርአያ ናቸው:: ይኸዉም ለህዝቦቻቸው «እኛ ከናንተና ከዚያ ከአላህ ሌላ ከምትገዙት ጣዖታት ሁሉ ንጹሆች ነን:: በእናንተም ካድን:: በአላህ አንድነት እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ::» ባሉ ጊዜ ኢብራሂም ለአባቱ፡- «ላንተ ከአላህ ቅጣት ምንም የማልጠቅምህ (የማላድንህ) ስሆን ላንተ በእርግጥ ምህረትን እለምንልሃለሁ::» ማለቱ ብቻ ሲቀር «ጌታችን ሆይ ባንተ ላይ ተመካን ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው::» (ባለው ተከተሉ።)
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበኢብራሂምና በእነዚያ ከእርሱ ጋር በነበሩት (ምእምናን) መልካም መከተል አለቻችሁ፡፡ ለሕዝቦቻቸው «እኛ ከእናንተ ከአላህ ሌላ ከምትግገዙትም ንጹሖች ነን፡፡ በእናንተ ካድን፡፡ በአላህ አንድ ብቻ ሲኾን እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ፡፡» ባሉ ጊዜ (መልካም መከተል አለቻችሁ)፡፡ ኢብራሂም ለአባቱ «እኔ ለአንተ ከአላህ (ቅጣት) ምንም የማልጠቅም ስኾን ለአንተ በእርግጥ ምሕረትን እለምንልኻለሁ» ማለቱ ብቻ ሲቀር፡፡ «ጌታችን ሆይ! በአንተ ላይ ተመካን፡፡ ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው፤» (ባለው ተከተሉት)፡፡......
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70