يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ إِذَا جَآءَكَ ٱلْمُؤْمِنَٰتُ يُبَايِعْنَكَ عَلَىٰٓ أَن لَّا يُشْرِكْنَ بِٱللَّهِ شَيْـًٔا وَلَا يَسْرِقْنَ وَلَا يَزْنِينَ وَلَا يَقْتُلْنَ أَوْلَٰدَهُنَّ وَلَا يَأْتِينَ بِبُهْتَٰنٍ يَفْتَرِينَهُۥ بَيْنَ أَيْدِيهِنَّ وَأَرْجُلِهِنَّ وَلَا يَعْصِينَكَ فِى مَعْرُوفٍ فَبَايِعْهُنَّ وَٱسْتَغْفِرْ لَهُنَّ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy12. አንተ ነብይ ሆይ! ምዕመናቶቹ በአላህ ምንም ላያጋሩ፤ ላይሰርቁ፤ ላያመነዝሩ፤ ልጆቻቸውን ላይገድሉ፤ በእጆቻቸውና በእግሮቻቸው መካከል ኃጢአትን ላያመጡ (ላይሰሩ)፤ በበጎም ስራም ትዕዛዝን ላይጥሱ ቃል ኪዳን ሊገቡልህ ወደ አንተ በመጡ ጊዜ ቃል ኪዳን ተጋባቸው:: ለእነርሱም አላህን ምህረት ለምንላቸው:: አላህ በጣም መሀሪና እጂግ በጣም አዛኝ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአንተ ነቢዩ ሆይ! ምእምናቶቹ በአላህ ምንንም ላያጋሩ፣ ላይሰርቁም ላያመነዝሩም፣ ልጆቻቸውን ላይገድሉም፣ በእጆቻቸውና በእግሮቻቸው መካከልም የሚቀጣጥፉት የኾነን ኃጢኣት ላያመጡ (ላይሠሩ) በበጎም ሥራ ትዕዛዝህን ላይጥሱ ቃል ኪዳን ሊገቡልህ በመጡህ ጊዜ ኪዳን ተጋባቸው፡፡ ለእነርሱም አላህን ምሕረት ለምንላቸው፡፡ አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡