caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 6

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:6

أَلَمْ يَرَوْا۟ كَمْ أَهْلَكْنَا مِن قَبْلِهِم مِّن قَرْنٍ مَّكَّنَّٰهُمْ فِى ٱلْأَرْضِ مَا لَمْ نُمَكِّن لَّكُمْ وَأَرْسَلْنَا ٱلسَّمَآءَ عَلَيْهِم مِّدْرَارًا وَجَعَلْنَا ٱلْأَنْهَٰرَ تَجْرِى مِن تَحْتِهِمْ فَأَهْلَكْنَٰهُم بِذُنُوبِهِمْ وَأَنشَأْنَا مِنۢ بَعْدِهِمْ قَرْنًا ءَاخَرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy6. ከበፊታቸው ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች መካከል ብዙዎቹን ማጥፋታችንን አላዩምን? ለእናንተ ያላስመቸነውን ለእነርሱ በምድር ውስጥ አስመቸናቸው:: በእነርሱም ላይ ዝናብን የተከታተለ ሲሆን ላክን:: ወንዞችንም በስራቸው እንዲፈሱ አደረግን:: በኃጢአቶቻቸዉም ምክንያት አጠፋናቸው:: ከኋላቸዉም ሌሎችን ሰዎች በየክፍለ ዘመኑ አስገኘን::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከበፊታቸው ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን ማጥፋታችንን አላዩምን ለእናንተ ያላስመቸነውን (ለእነርሱ) በምድር ውስጥ አስመቸናቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ዝናምን የተከታተለ ሲኾን ላክን፡፡ ወንዞችንም በሥራቸው እንዲፈሱ አደረግን፡፡ በኃጢአቶቻቸውም አጠፋናቸው፡፡ ከኋላቸውም ሌሎችን የክፍለ ዘመን ሰዎች አስገኘን፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70