قُلْ إِنِّى عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّى وَكَذَّبْتُم بِهِۦ مَا عِندِى مَا تَسْتَعْجِلُونَ بِهِۦٓ إِنِ ٱلْحُكْمُ إِلَّا لِلَّهِ يَقُصُّ ٱلْحَقَّ وَهُوَ خَيْرُ ٱلْفَٰصِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እኔ ከጌታዬ በመጣልኝ ግልጽ ማስረጃ ላይ ነኝ:: እናንተ ግን በእርሱ አስተባበላችሁ:: ያ የምትቻኮሉበት ቅጣት ውሳኔ እኔ ዘንድ አይደለም:: ፍርዱ ለአላህ ብቻ ነው:: አላህ እውነቱን ይፈርዳል:: እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነውና።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«እኔ ከጌታዬ በኾነች ግልጽ ማስረጃ ላይ ነኝ፡፡ በእርሱም አስተባበላችሁ፡፡ በርሱ የምትቻኮሉበት ቅጣት እኔ ዘንድ አይደለም፡፡ ፍርዱ ለአላህ ብቻ ነው፡፡ እውነትን ይፈርዳል፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው» በላቸው፡፡